
የምዕራብ ጉጂ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል። በምዕራብ ጉጂ ዞን የቡሌ ሆራ ከተማ ደም ባንክ ማዕከል ማስተባበሪያ እንደገለጸው ÷ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ደም የለገሱት ሴቶች፣ ወጣቶችና እናቶች ናቸው።
ደም የለገሱት በጎ ፈቃደኞች ለመከላከያ ሠራዊቱ በኋላ ደጀንነት የሚያደርጉት ሁለንተናዊ ድጋፍና ትብብር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የደም ባንክ ማዕከሉ ኃላፊ ተወካይ አቶ ሀብታሙ ኃይሉ ÷ በግል ፍላጎትና ተነሳሽነት ደም የለገሱት 63 በጎ ፈቃደኛ ሴት ወጣቶችና እናቶች ብቻ እንደሆኑ አስታውቀዋል፡፡
ከምዕራብ ጉጂና ቦረና ዞኖች ከበጎ ፈቃደኞች ደም የሚያሰባስቡ 34 የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች መሰማራታቸውን ገልጸዋል፡፡ከዞኖቹ ሞያሌ፣ ቡሌ ሆራ፣ ያቤሎ ተልተሌ፣ አባያና መልካ ሶዳ ከተሞችና ወረዳዎች ከበጎ ፈቃደኞች 3ሺህ ዩኒት ደም ለማሰባሰብ እየተሰራ ነው ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡ብርተኛው ህወሓት በንጹሀን ላይ ያደረሰው ጥቃት በፈጠረው መነሳሳት ባለፉት ሶስት ወራት በ85 በጎ ፈቃደኞች 85 ዩኒት ደም መለገሱን አስታውሰዋል፡፡