
በኢትዮጵያ እና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፣ እውነትን ለዓለም ለመግለጥ እያደረጋችሁ ያላችሁት ተጋድሎ እጅግ የሚደነቅ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል ።
ይህ ጥንታዊ ህዝብ በሩቅ እና በቅርብ ሃይሎች የተጋረጠበትን የህልውና ስጋት በአንድነት ማሸነፍ እንችላለን ብለዋል በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው።እንደ አድዋ ልጆች ኢትዮጵያን በጽናት ወደፊት እናሻግራታለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።