የወገን ጦር ጠላትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት በሚያስችል ቁመና ላይ ይገኛል – የክተት ጥሪ ዘማቾች

አሸባሪውን የትህነግ ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ የወገን ጦር በዋግኽምራ ግንባር በጀግንነት በመፋለም ላይ ይእንደሚገኝና ወራሪው ኃይል ሳይደመስስ እንደማይመለሱ በግንባሩ የክተት ጥሪ ዘማቾች ገልጸዋል።

የወገን ጦር ጠላትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል። የክተት ጥሪ ዘማች አብዩ ታረቀኝ የክተት ጥሪውን ተቀብለው አሸባሪውን ወራሪ ኃይል ለመፋለም በዋግ ግንባር ተገኝተዋል።

አሸባሪውና ወራሪው ቡድን እስኪደመሰስ በቁርጠኝነት እንደሚፋለሙ ነው የገለጹት። ወጣቶች ግንባር ድረስ በመዝመት ከጠላት ጋር ከመፋለም ባለፈ በስንቅ ዝግጅትና በሌሎች ሎጀስቲክስ አቅርቦት ትግሉን ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጭ አሌ መልካሙ እንዳለው ፥ ወራሪው የትህነግ ኃይል በአማራ ላይ በፈጸመው ግድያ፣ ሀብት ዘረፋና ውድመት ወደ ግንባር እንዲዘምት አስገድዶታል።መኖር የሚቻለው ሀገር ሲኖር በመሆኑ አሸባሪና ወራሪ ኃይሉን ሳይደመሰስ እንደማይመለስ ነው የተናገረው። የክተት ጥሪ ዘማች ሻንበል ፈቃዱም እንዲሁ ፥ ኢትዮጵያን ካጋጠማት የህልውና አደጋ ለመታደግ ከወንድማቸው ጋር ወደ ግንባር መዝመታቸውን ተናግረዋል።

ሀብት እና ንብረት ማፍራት፣ ቤተሰብም መምራት የሚቻለው ሀገር ሰላም ሲሆን እንደሆነ ያነሱት ዘማቹ ፥ ወጣቶች በአማራ ላይ እየደረሰ ያለውን ሞት፣ መፈናቀል እና ዘረፋ ለማስቆም ሁለገብ ትግል ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Next Post

አደራዳሪዎቹ ለነ ደብረፂዮን እጅ እንዲሠጡ

Sun Nov 21 , 2021