የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ስዋሂሊ ቋንቋ ተጨማሪ የህብረቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ወሰኑ።መሪዎቹ ውሰኔው ያሳለፉት ላለፉት ቀናት በአህጉሪቱ መዲና አዲስ አበባ በተካሄደው 35ኛ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ መሆኑም ታውቋል።
መሪዎቹ ከውሳኔው ላላ የደረሱት የታንዛንያው ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ፊሊፕ ምፓንጎ ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ እንደሆነም ነው የተገለጸው።ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ የስዋሂሊ ቋንቋ በአፍሪካ ከ100 ሚልየን በላይ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ መሆኑን በ35ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለተሳተፉ መሪዎች ገልጸዋል።
35ኛ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተሳተፉ የሀገራት መሪዎችም ስሃዋሂሊ ቋንቋን 5ኛ የህብረቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ወስነዋል።የአፍሪካ ህብረት እስካሁን አረብኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረነሳይኛ፣ ፖርቹጋል እና ስፓኒሽ ቋንቋዎችን የስራ ቋንቋ አድርጎ በመጠቀም ላይ ይገኛል።