
“ዘላለም ሙላቱ በሕግ እንዲጠየቁ የማሟያ ምርጫ እንዲካሄድ ባልደራስ ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ አስገባ ገዥውን ፓርቲ በመወከል የአዲስ አበባ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልና የትምህርት ቢሮ ሓላፊ የሆኑት ዘላለም ሙላቱ፣ የከተማዋ ምክር ቤት የካቲት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ላይ ባሰሙት ንግግር፣” በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኘው የኦሮሚያ ልዩ ዞን ፣አዲስ አበባ ከርሷን ሞልታ ፈርሷን የምትጥልባቸው ናቸው” በማለት በአደባባይ ሕዝብን ዘልፈዋል። ይህን ተከትሎ፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ዘላፊው ከሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልነታቸው የሚነሱበትንና የማሟያ ምርጫ የሚደረግበትን እንቅስቃሴ ጀምሯል።
በዚህም መሠረት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሂደቱን የማስጀመሪያ ሕጋዊ ድጋፍ እንዲሰጠው ባልደራስ ጠይቋል። የጥያቄውን ሙሉ መልዕክት የያዘ ደብዳቤም ዛሬ ሰኞ የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በፕሬዚደንቱ እስክንድር ነጋ እና በአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በኩል የቦርዱ ዋና ጽ/ቤት በአካል ተኝተው አቅርበዋል።