
በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስና የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባለት የጋራ ውይይት ላይ ቤተክርስቲያን ያቀረበቻቸው ጥያቄዎች ሁሉ ላይ ለመነጋገር በከተማ አስተዳደሩ በኩል ተቀባይነት ያገኙ ሆነዋል። ችግሩንም በመሰረቱና በማያዳግም መልኩ መፍታት እንደሚገባም በጋራ ታምኖበታል ስለሆነም ችግሮቹን በማያዳግም ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መልኩ መፍታት ይቻል ዘንድ ቋሚ ሲኖዶስና የከተማ አስተሩ መግባባት ላይ የደረሱ ሲሆን በቤተክርስቲያን የቀረቡ ዝርዘር ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ እያንዳንዱ ጥያቄዎች ምላሽ እየተሰጠበት እንደሚሔድና ጎን ጉንም ቤተክርስቲያን እና የከተማ አስተዳደሩ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል። የጋራ መግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።