አሸባሪውን የትህነግ ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ የወገን ጦር በዋግኽምራ ግንባር በጀግንነት በመፋለም ላይ ይእንደሚገኝና ወራሪው ኃይል ሳይደመስስ እንደማይመለሱ በግንባሩ የክተት ጥሪ ዘማቾች ገልጸዋል። የወገን ጦር ጠላትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል። የክተት ጥሪ ዘማች አብዩ ታረቀኝ የክተት ጥሪውን ተቀብለው አሸባሪውን ወራሪ ኃይል ለመፋለም በዋግ ግንባር ተገኝተዋል። አሸባሪውና ወራሪው […]

በባቲ ካሳጊታ ግንባር ያለ የሌለ ዐቅሙን ሰብስቦ የመጣው የጠላት ኃይል ለወሬ ነጋሪ እንዳይተርፍ ሆኖ ተደመሰሰ። የጠላት አርሚ 4 የተባለው ሠራዊት ከነ ተደራቢ ኃይሉ ሳምንት ሙሉ ሲቀጠቀጥ ከርሞ በዛሬው ዕለት ቀኑን ሙሉ በፈጀ ውጊያ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በአናብስቱ የአፋር ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አከርካሪው ተሰብሯል። በዚህ አስደናቂ ውጊያ ጀግኖቹ ባደረጉት ተጋድሎ፣ ጠላት […]

ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ይህንን ጊዜያዊ ማዕበል ከፍለን በአንድነት እንድናቋርጠው እጠይቃለሁ ሲሉ ጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ለኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሀገሪቱ ውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ሥጋቶችን ስትጋፈጥ ብዙ ትግሎች እና ምቾት ማጣት ይኖርብናል ብለዋል። ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ይህንን ጊዜያዊ ማዕበል ከፍለን በአንድነት እንድናቋርጠውም ጠይቀዋል። በአንድነት […]

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የትኛውንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደምታወግዝ ገለጸች፡፡ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፌ ሉቱንዱላ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸው በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሚስተዋለውን ግጭት ለመፍታት ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንኮ እና የአፍሪካ ህብረት ሊኖራቸው በሚችለው ሚና ዙሪያ መክረዋል፡፡ ክርስቶፌ […]

በኢትዮጵያ እና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፣ እውነትን ለዓለም ለመግለጥ እያደረጋችሁ ያላችሁት ተጋድሎ እጅግ የሚደነቅ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል ። ይህ ጥንታዊ ህዝብ በሩቅ እና በቅርብ ሃይሎች የተጋረጠበትን የህልውና ስጋት በአንድነት ማሸነፍ እንችላለን ብለዋል በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው።እንደ አድዋ ልጆች ኢትዮጵያን በጽናት ወደፊት እናሻግራታለን ብለዋል ጠቅላይ […]

የአሜሪካ መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግሥት መደገፍ አለበት ሲሉ በኢትዮጵያ ለጉብኝት የመጡት አሜሪካዊቷ ሜሊሳ ዳቢ ገለጹ። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት አሜሪካዊቷ ሜሊሳ ዳቢ ÷ የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ከመጣል መቆጠብ እንዳለበትም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በህዝብ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ በተካሄደ ምርጫ ወደ ሥልጠን የመጣው መንግሥት ላይ ማዕቀብ መጣል […]

የምዕራብ ጉጂ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል። በምዕራብ ጉጂ ዞን የቡሌ ሆራ ከተማ ደም ባንክ ማዕከል ማስተባበሪያ እንደገለጸው ÷ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ደም የለገሱት ሴቶች፣ ወጣቶችና እናቶች ናቸው። ደም የለገሱት በጎ ፈቃደኞች ለመከላከያ ሠራዊቱ በኋላ ደጀንነት የሚያደርጉት ሁለንተናዊ ድጋፍና ትብብር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የደም ባንክ ማዕከሉ ኃላፊ […]