
ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ይህንን ጊዜያዊ ማዕበል ከፍለን በአንድነት እንድናቋርጠው እጠይቃለሁ ሲሉ ጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ለኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሀገሪቱ ውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ሥጋቶችን ስትጋፈጥ ብዙ ትግሎች እና ምቾት ማጣት ይኖርብናል ብለዋል።
ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ይህንን ጊዜያዊ ማዕበል ከፍለን በአንድነት እንድናቋርጠውም ጠይቀዋል። በአንድነት ከቆምን ማሸነፋችን ሰበር ዜና አይሆንም! ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ማሸነፍን ከዚህ በፊት አድርገነዋልና አሁንም እናደርገዋለን ብለዋል።