በባቲ ካሳጊታ ግንባር የጠላት ምሽግ ተሰበረ

በባቲ ካሳጊታ ግንባር ያለ የሌለ ዐቅሙን ሰብስቦ የመጣው የጠላት ኃይል ለወሬ ነጋሪ እንዳይተርፍ ሆኖ ተደመሰሰ። የጠላት አርሚ 4 የተባለው ሠራዊት ከነ ተደራቢ ኃይሉ ሳምንት ሙሉ ሲቀጠቀጥ ከርሞ በዛሬው ዕለት ቀኑን ሙሉ በፈጀ ውጊያ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በአናብስቱ የአፋር ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አከርካሪው ተሰብሯል። በዚህ አስደናቂ ውጊያ ጀግኖቹ ባደረጉት ተጋድሎ፣ ጠላት ሲተማመንባቸው የነበሩትን ሁለት ስትራቴጂካዊ ተራሮች ምሽጎቹን በመስበር ተቆጣጥሯል።

በዚህ ሰሞን ዉጊያ ጠላት ሚሌ እገባለሁ በሚል የሰበሰባቸው በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎቹና ጀሌዎቹ ተደምስሰውበታል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማርከዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች፣ በርካታ ስናይፐሮችና መትረየሶች ተማርከዋል። ጠላት በዚህ ግንባር ከደረሰበት ውድመት የዛሬው እጅግ ዘግናኝ መሆኑ ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Next Post

የወገን ጦር ጠላትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት በሚያስችል ቁመና ላይ ይገኛል – የክተት ጥሪ ዘማቾች

Sun Nov 21 , 2021
አሸባሪውን የትህነግ ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ የወገን ጦር በዋግኽምራ ግንባር በጀግንነት በመፋለም ላይ ይእንደሚገኝና ወራሪው ኃይል ሳይደመስስ እንደማይመለሱ በግንባሩ የክተት ጥሪ ዘማቾች ገልጸዋል። የወገን ጦር ጠላትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል። የክተት ጥሪ ዘማች አብዩ ታረቀኝ የክተት ጥሪውን ተቀብለው አሸባሪውን ወራሪ ኃይል ለመፋለም በዋግ ግንባር ተገኝተዋል። አሸባሪውና ወራሪው […]