አሜሪካ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግሥት መደገፍ አለበት- አሜሪካዊቷ ሜሊሳ ዳቢ

የአሜሪካ መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግሥት መደገፍ አለበት ሲሉ በኢትዮጵያ ለጉብኝት የመጡት አሜሪካዊቷ ሜሊሳ ዳቢ ገለጹ። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት አሜሪካዊቷ ሜሊሳ ዳቢ ÷ የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ከመጣል መቆጠብ እንዳለበትም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በህዝብ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ በተካሄደ ምርጫ ወደ ሥልጠን የመጣው መንግሥት ላይ ማዕቀብ መጣል ተገቢም፣ ፍትሃዊም አይደለም ብለዋል። አሜሪካዊያኖች ኢትዮጵያን ይወዳሉ ነገር ግን በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ መረዳት የሚችሉበት ትክክለኛ መረጃ እያገኙ አለመሆኑንም ዳቢ ጠቅሰዋል።

ሲ ኤን ኤን፣ ቢ ቢ ሲ፣ አልጀዚራና ሌሎችም ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ኢትዮጵያን በተመለከተ የሐሰት መረጃ እያስተላለፉ መሆኑንም ተናግረዋል።በዚህም ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ሰግተው እንደነበር ገልጸው ÷ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ሚዲያዎቹ ያሰራጩት መረጃ ትክክል አለመሆኑን መረዳታቸውን ተናግረዋል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በርካታ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መፈጸሙን ጠቁመው ምዕራባውያኑ ከአሸባሪው ቡድን ጋር መቆማቸው ግርምት እንደጫረባቸው ገልጸዋል። አሸባሪው ህወሓት በንጹሃን ላይ ከፍተኛ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እየፈጸመ መሆኑን ጠቁመው ÷ ኢትዮጵያ ሰላም እንዳይኖራት የሚሰራ መሆኑን ነው ያስረዱት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Next Post

የተጋረጠብንን የህልውና ስጋት በአንድነት እናሸንፋለን – ጠ/ሚ ዐቢይ

Sun Nov 21 , 2021
በኢትዮጵያ እና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፣ እውነትን ለዓለም ለመግለጥ እያደረጋችሁ ያላችሁት ተጋድሎ እጅግ የሚደነቅ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል ። ይህ ጥንታዊ ህዝብ በሩቅ እና በቅርብ ሃይሎች የተጋረጠበትን የህልውና ስጋት በአንድነት ማሸነፍ እንችላለን ብለዋል በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው።እንደ አድዋ ልጆች ኢትዮጵያን በጽናት ወደፊት እናሻግራታለን ብለዋል ጠቅላይ […]