ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአትዮጵያ ላይ የሚደረግን ጣልቃ ገብነት እንደምታወግዝ ገለጸች

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የትኛውንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደምታወግዝ ገለጸች፡፡ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፌ ሉቱንዱላ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሚስተዋለውን ግጭት ለመፍታት ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንኮ እና የአፍሪካ ህብረት ሊኖራቸው በሚችለው ሚና ዙሪያ መክረዋል፡፡ ክርስቶፌ ሉቱንዱላ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ከሆኑት ፌሌክስ ሺሴኬዲ የተላከ መልዕክትን ለአቶ ደመቀ አድርሰዋል፡፡

በዚህም ፕሬዚዳንት ፌሌክስ ሺሴኬዲ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታን በቅርበት እየተከታተሉ እንደሆነ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሀገራቸው ለኢትዮጵያ ሰላም መስፈን ያላትን አጋርነት እና ወንድማማችነት ለማሳየት የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ያካተተ ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውን ገልጸዋል። ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የትኛውንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደምታወግዝ መናገራቸውም በመልዕክቱ ተመላክቷል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው÷ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለኢትዮጵያ ሰላም መስፈን ያሳየችውን ተነሳሽነት አድንቀው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና የአፍሪካ ሕብረት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ሊያይዋቸው የሚገባውን ወሳኝ ጉዳዮች አንስተዋል።

ለሰብዓዊ ድጋፍ መዳረስና ለዘላቂ ሰላም መስፈን መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ቢያደርግም አሸባሪው ህወሃት ግን ተኩስ አቁሙን በመጣስ ወረራ መፈጸሙን አስታውሰዋል፡፡

“አሸባሪውና ወራሪው ህወሃት በአፋርና አማራ ክልሎች በሚያካሂደው ወረራና ግፍ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃና ደም መፍሰስ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በግልጽና በማያሻማ መልኩ እንድታወግዘው ያስፈልጋል” ነው ያሉት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Next Post

ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ይህንን ጊዜያዊ ማዕበል ከፍለን በአንድነት እናቋርጠው – ጠ/ሚ ዐቢይ

Sun Nov 21 , 2021
ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ይህንን ጊዜያዊ ማዕበል ከፍለን በአንድነት እንድናቋርጠው እጠይቃለሁ ሲሉ ጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ለኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሀገሪቱ ውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ሥጋቶችን ስትጋፈጥ ብዙ ትግሎች እና ምቾት ማጣት ይኖርብናል ብለዋል። ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ይህንን ጊዜያዊ ማዕበል ከፍለን በአንድነት እንድናቋርጠውም ጠይቀዋል። በአንድነት […]