
በወለጋ ሆሮጉዱሩ ዞን አሙሮ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጥቂዎች ከባድ ጥቃት መክፈታቸው ተሰማ። በተከፈተው ጥቃት ምን ያህል ንጹህ ሰዎች እንደተገደሉ አልታወቀም። በወረዳው በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ በተከፈተ ጥቃት በርካቶች ተገድለዋል። በአከባቢው የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ኃይል ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዱ ከጥቃቱ ያመለጡ ሰዎች ይናገራሉ። በርካታ ሰዎች ጥቃቱን ሸሽተው ወደ ጫካ ገብተው መሸሸጋቸው ታውቋል።
ጉተን ቀበሌ ያለው የመከላከያ ኃይልና የኦህዴድ ብልጽግና አመራሮች የአከባቢውን አርሶ አደሮች መሳሪያ እንዲያስረክቡ መጠየቁ የተሰማ ሲሆን አርሶ አደሮቹ ሰላም ባልወረደበት ንጽሃን እያላቁ ባሉበት ወቅት መሳሪያ አስረክቡ መባሉ ተቀባይነት የለውም በማለት ስብሰባውን ጥለው መውጣታቸው ታውቋል። አርሶ አደሩ ይህንን እርምጃ በመውሰዱ የተበሳጩ አመራሮች አማራውን እናስፈጀዋለን በማለት እየዛቱ ይገኛሉ። ይህን ተከትሎ ከባድ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል በሚል በአከባቢው ውጥረት ነግሷል።