
የምክር ቤቱ ጉባኤ አፈ ጉባኤ ቡዜና አልቃድር በመክፈቻ ንግግር በይፋ አስጀምረዋል።ምክር ቤቱ በሁለት ቀን ቆይታው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከንቲባ ጽሕፈት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከተማ የአስተዳደሩን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምን ቅድሚያ ሰጥቶ የሚገመግም ሲሆን የአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች የስድስት ወራት አፈጻጸም፣ የመሬት ይዞታ ማስለቀቅ እና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ ተወያይቶ ማጽደቅ እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶችን ማጽደቅ የምክር ቤቱ አጀንዳዎች ናቸው ተብሏል፡፡